Перейти к содержимому

ፀጉሬን ያሳደገልኝ የቫዝሊን የበቆሎ ዱቄት እና የቤቢኦይል ታምር/haircare/haircut/hairstyle

Roza ጉራጌ

0:00 / 0:00

ፀጉሬን ያሳደገልኝ የቫዝሊን የበቆሎ ዱቄት እና የቤቢኦይል ታምር/haircare/haircut/hairstyle

9 957 просмотров · 2 дня назад
Roza ጉራጌ
236 тыс. подписчиков
9 957 просмотров · 2 дня назад
በዛሬው ቪዲዮ ፀጉራችሁ በፍጥነት እንዲያድግ፣ እንዳይሰባበር፣ እንዳይነቃቀል እና እጅግ በጣም እንዲለሰልስ የሚረዳ ድንቅ የተፈጥሮ የፀጉር ማስክ (ኮንዲሽነር) አሰራርና አጠቃቀም ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ይህ ውህድ ያለ ምንም ከፍተኛ ወጪ እና ከኬሚካል ነፃ በሆኑ የቤት ውስጥ ግብዓቶች የሚዘጋጅ ሲሆን፣ በተለይ ለደረቀና ለከርዳዳ ፀጉር ተአምራዊ ለውጥ ያመጣል! 🌿 የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (Ingredients) ውሃ – 2 ብርጭቆ ቅርንፉድ – 1 የሾርባ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት – 1 የሾርባ ማንኪያ የበቆሎ ዱቄት (ነሻ) – 2 የሾርባ ማንኪያ ቫዝሊን (ካልተመቻችሁ ተልባ፣ የወይራ ዘይት ወይም የኮኮናት ዘይት) ቤቢ ኦይል (ወይም ያላችሁ የተፈጥሮ ዘይት) 📝 አጠቃቀም (How to Use) ውህዱን ካዘጋጃችሁ በኋላ ከፀጉራችሁ ስር እስከ ጫፍ ድረስ በደንብ ተቀቡት። የራስ ቆዳችሁን ለ5 ደቂቃ ያህል በጣቶቻችሁ ቀስ እያደረጋችሁ ማሳጅ አድርጉት። በላስቲክ (ሻወር ካፕ) ሸፍናችሁ ለ 1 ሰዓት ያህል አቆዩት። በመጨረሻም በሻምፖ ታጥባችሁ፣ ፀጉራችሁ እርጥብ እያለ ጫፍ ጫፉን ዘይት በመቀባት ተንከባከቡት። #haircare #ethiopianyoutuber #hairgrowth #diyhairmask #roza #የፀጉርእንክብካቤ