Ethiopian Rice Dish ጣፋጭ ሩዝ
Melegna | መለኛ
0:00 / 0:00
Ethiopian Rice Dish ጣፋጭ ሩዝ
27 338 просмотров · 7 месяцев назад
Melegna | መለኛ
190 тыс. подписчиков
27 338 просмотров · 7 месяцев назад
ሩዝ በቲማቲም ስልስ
ይህን የሩዝ አይነት ላለንበት የዐብይ ፆም እና ለመጪው የረመዳን ፆም ከሌሎች ምግቦች ጋር እንደ አይነት ካልሆነ ደግሞ ብቻውን አቅርባችሁ መመገብ ትችላላችሁ፡፡ በጣም ጣፋጭ እና ቶሎ የሚደርሱ የሩዝ አይነቶች መካከል አንዱ ነው ፡፡ ሩዙን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ የግብዓት አይነቶች እና መጠቀም ያለባችሁን የማጣፈጫ ቅመም አይነቶች ዝርዝር ከስር አቅርበናል፡፡
የግብዓት አይነት እና መጠን
ሩዙን ለመቀቀል
2ኩባያ ሩዝ
4-6 ኩባያ ውሃ ሩዙን ለመቀቀል
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
ሩዙን ስትቀቅሉ እንደ ቀረፋ ፣ ቅሩንፉድ እና የተለያዩ የሩዝ ደረቅ ቅመሞችን አብራችሁ ጨምራችሁ መቀቀል ትችላላችሁ
ስልሱን ለማዘጋጀት
2 ልጅ የሆነ ካሮት
2 ድንች
2 ራስ ቀይ ሽንኩርት
8 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ፍሬ ዝንጅብል
1 ተለቅ ያለ ብስል ቲማቲም
2 የሾርባ ማንኪያ ሶይ ሶስ
2 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
የቲማቲም ድልሁ ለስልሱ መጣፈጥ ዋነኛ ግብዓት ስለሆነ መጨመር እንዳትዘነጉ
የምትፈልጉትን ያህል ጨው
የጨው ምጣኔያችሁ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቹሃል
የምትጠቀሙት ሶይ ሶስ በውስጡ በጣም ከፍተኛ የጨው መጠን ስላለው እና ሩዙን ለመቀቀል ጨው ስለምትጠቀሙ የምትጨምሩትን የጨው መጠን ቀምሳችሁ እንድትጨምሩ እንመክራለን
የማጣፈጫ ቅመሞች
1 የቡና ማንኪያ ሮዝሜሪ
1 የቡና ማንኪያ ቀረፋ
1 የቡና ማንኪያ የነጭ ሽንኩርት ዱቄት
ግማሽ የቡና ማንኪያ ጥቁር ቁንዶ በርበሬ
ማባያ
ቂጣ
ዳቦ