Перейти к содержимому

አብዮቱ ሲያብጥና ሲቀጣጠል ክፍል 22 ካለፈው የቀጠለ

የታሪክ አለም(History world)

0:00 / 0:00

አብዮቱ ሲያብጥና ሲቀጣጠል ክፍል 22 ካለፈው የቀጠለ

105 просмотров · 3 недели назад
የታሪክ አለም(History world)
320 подписчиков
105 просмотров · 3 недели назад
በዚህ የትረካ ቪዲዮ:- *የጀብሃ አባላት በተማሪዎች ማህበራት ውስጥ ሰርገው በመግባት ማህበራቱን በአዲስ መልክ ማዋቀራቸውና የራሳቸውን ሰው የማህበራቱ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን *የተማሪዎች አመጽ እየተጋጋለ መሄዱ ያሳሰበው ዘውዳዊ መንግስት የተለያዩ የማስጠንቀቂያ አዋጆችን በመደንገግና በፀጥታ ሃይሎቹ እርምጃ በመውሰድ አመጹን ለማርገብ ቢሞክርም አመጹ ይበልጥ ከመጋል በቀር እንዳልበረደ *ተደብቆ የነበረው የ1965ቱ ረሃብ ይፋ ከወጣ በኋላ ከተማሪዎች አልፎ ሌሎች አካላትም ስርዓቱን ተቃውመው እንደተነሱ *ከዚህ በኋላ መምህራን ሾፌሮች ወታደሮችና ሌሎችም በስርዓቱ ላይ አምጸው መነሳታቸውን *የታክሲ ሾፌሮች የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን አስመልክቶ የስራ ማቆም አድማ እንዳደረጉ *የነገሌ ቦረና ወታደሮችም የምንበላው ምግብና የምንጠጣው ውሃ ከአፈር ጋር ተደባለቀብን በማለት አምጸው አዛዦቻቸውን እስከማሰር እንደደረሱ የመምህራን ማህበርም መንግስት ሊተገብር ያሰበውን የትምህርት ፖሊሲ ሴክተር ሪቪውን አስመልክቶ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ እንዳደረጉ *በኤርትራ አስመራ የሚገኘው ሁለተኛው ክ/ጦር ሰራዊቶች አምጸው በመነሳት አየር ማረፊያን ሬዲዮ ጣቢያና ቁልፍ ስፍራዎችን ተቆጣጥረው በራዲዮ ጥያቄያቸውን ለጃንሆይ ማቅረባቸውም *ጃንሆይም ሰራዊቶቹ ላቀረቧቸው አብዛኞቹ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠታቸውንና የነገሌ ቦረና ሰራዊት አበላት አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን *ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀ/ወልድ ወርደው በምትካቸው ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውንና ካቢኔውም በአዲስ መልክ መዋቀሩን *ካቢኔው ፈጣን የማሻሻያ እርምጃዎችን ቢወስድም ህዝቡ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም በማለት አመጹን ይበልጥ ማጋጋሉን *ህዝቡ ሰራዊቱ የራሱን ጥቅም አስከብሮ ስለህዝቡ ብሶት አያገባኝም አለ እየተባለ በመወረፉ ወታደሩ ወዳላሰበውና ወዳልፈለገው ስልጣን እንዲያመራ መንገድ እንደተጠረገለት *ህዝባዊውን አመጽ የሚያስተባብር የተደራጀ ፖለቲካዊ ፓርቲ ወይም ድርጅት ባለመኖሩ ወታደሩ ህዝቡን አስተባብሮ ስልጣን ለመያዝ ቀላል እንደሆነለትና ለዚህም ወታደሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ መጀመሩን እናዳምጣለን *ይሄ ስለ 1966 አብዮት የሚተርከው ቪዲዮ ሰፊና ዝርዝር መረጃ ስለሚሰጣችሁ ሙሉውን የቪዲዮ ትረካ በጥሞናና በትዕግስት እንድትከታተሉና እንድታዳምጡ በትህትና እንጠይቃችኋለን *ቻናላችንንም ሰብስክራይብ ላይክ ሼርና ፎሎው እያደረጋችሁ ታሪካዊ ቪዲዮዎችን በማዳመጥ እውቀታችሁን አዳብሩ የግንዛቤ አድማሳችሁንም አስፉ