ሆቴል ውስጥ በጣም ውድ የሆነውን ምግብ በቤት ውስጥ በቀላሉ
ጤናማ ምግብ Tenama Migib
0:00 / 0:00
ሆቴል ውስጥ በጣም ውድ የሆነውን ምግብ በቤት ውስጥ በቀላሉ
299 просмотров · 4 дн. назад
ጤናማ ምግብ Tenama Migib
910 подписчиков
299 просмотров · 4 дн. назад
ሰላም ውድ እና የተከበራችሁ የ ጤናማ ምግብ Tenama Migib ቤተሰቦች!
ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት በሆቴሎች ውስጥ እጅግ በጣም ውድ የሆነውን ምግብ፣ በቤታችን ውስጥ በቀላሉ እና በጣም በሚጣፍጥ መልኩ የምናዘጋጅበትን ለየት ያለ የስኳር ድንች እና የዶሮ አሰራር ነው። ለየት ያለ ጣዕም ያለው፣ ለጤና ተስማሚ እና ለማንኛውም ፕሮግራም የሚሆን ምርጥ የምግብ አሰራር ነው፤ ሰርታችሁ ሞክሩት ትወዱታላችሁ!
ቪዲዮውን ከወደዳችሁት Like እና ለወዳጅ ዘመድዎ Share ማድረጋችሁን አትርሱ። እንዲሁም ለዚህ ቻናል አዲስ ከሆናችሁ ደንበኛ ለመሆን Subscribe በማድረግ የደወል ምልክቷን ይጫኑ። ሀሳብ አስተያየታችሁንም በኮሜንት ላይ አካፍሉኝ!
የአሰራር ሂደት በደቂቃ (Timestamps):
00:00 - መግቢያ
01:07 - የድንች እና የስኳር ድንች ዝግጅትና አቀቃቀል
02:46 - ድንቹን ማለስለስና ቅመሞችን መጨመር
03:33 - የዶሮውን ስጋ ማዘጋጀትና መጥበስ
04:47 - ሽንኩርትና አትክልቶችን ከዶሮው ጋር ማብሰል
07:11 - የክሬም እና የስፒናች ሶስ ዝግጅት
09:12 - ድንቹን መቅረጽ እና ግብዓቶቹን ማቀናጀት
10:09 - ቺዝ መጨመር እና በኦቭን (Oven) ውስጥ ማብሰል
10:28 - የመጨረሻ ውጤት እና ማጠቃለያ
የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (Ingredients):
ለድንች ዝግጅት፦
4 መካከለኛ ድንች እና 2 ስኳር ድንች
1 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
2 የሾርባ ማንኪያ የበቆሎ ዱቄት (Cornstarch)
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው፣ ቆንዶ በርበሬ እና የድምብላል ዱቄት (Coriander powder)
ለዶሮ እና አትክልቱ ዝግጅት፦
500 ግራም የዶሮ ስጋ (በትንንሹ የተከተፈ)
400 ግራም የተቀላቀለ አትክልት
1 ተለቅ ያለ ሽንኩርት እና 3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
1 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ እና 3 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
ቅመሞች፦ ኩዝባራ (ድምብላል)፣ ፓፕሪካ፣ እርድ፣ ኦሪጋኖ፣ ጨው እና ቆንዶ በርበሬ
ለሶስ (White Sauce) ዝግጅት፦
1 መካከለኛ ሽንኩርት እና 3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
400-500 ግራም ስፒናች (Spinach)
1 ኩባያ የኩኪንግ ክሬም (Cooking cream)
ቅመሞች፦ ኦሪጋኖ፣ ጨው፣ ቆንዶ በርበሬ፣ የተፈጨ ድምብላል
ሞዛሬላ ቺዝ (Mozzarella cheese)
#የምግብአሰራር #EthiopianFood #የዶሮአሰራር #ጤናማምግብ #ድንችበዶሮ