Перейти к содержимому

AI፣ ፈጠራ እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ | ሰለሞን ካሳ S2 EP8

MindseTube

0:00 / 0:00

AI፣ ፈጠራ እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ | ሰለሞን ካሳ S2 EP8

22 444 просмотра · 12 часов назад
MindseTube
181 тыс. подписчиков
22 444 просмотра · 12 часов назад
የዚህ ሳምንት እንግዳችን፣ የታዋቂው የቴሌቪዥን ፕሮግራም “TechTalk with Solomon” አዘጋጅና አቅራቢ፣ የቴክኖሎጂ አማካሪ እና ደራሲ ሰለሞን ካሳ ናቸው። ሰለሞን ውስብስብ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ጉዳዮችን ቀላልና ለሁሉም ተደራሽ በሆነ መንገድ በአማርኛ በማቅረብ፣ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ግንዛቤ እንዲያድግ ለዓመታት ሲሰሩ ቆይተዋል። ሰለሞን በሶፍትዌር ምህንድስና (Software Engineering) እና በቴክኖሎጂ አማካሪነት የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራማቸው፣ በጽሑፎቻቸውና በህዝባዊ መድረኮች ላይ በሚያደርጓቸው ንግግሮች የሳይንስና የቴክኖሎጂ እውቀት በተለይም ለወጣቱ ትውልድ እንዲደርስ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ከዚህም ባለፈ፣ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈጣሪዎችና የአዳዲስ ሀሳቦች አፍላቂዎች እንዲሆኑ በማበረታታት ይታወቃሉ። ይህ የውይይት ክፍል ከሰለሞን አዲስ መጽሐፍ፣ "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፦ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" ምረቃ ጋር በተያያዘ ለሁለት ዓመታት ባደረጉት ጥናትና የጽሑፍ ስራ ያዘጋጁትን መጽሐፍ፣ በዘመናችን ፈጣን ለውጥ እያመጣ ያለውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) በአማርኛ ለአንባቢያን ያቀርባል። የመጽሐፉ ርዕስም ለዘመናችን አንድ ወሳኝ ጥያቄ ያነሳል፦ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል፣ ወይስ የሰው ልጅን የፈጠራ ሚናን ያጠፋል? በዚህ ክፍል፣ የሰለሞንን የህይወትና የሙያ ጉዞ እንዲሁም ስለ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ያላቸውን አመለካከት እንዳስሳለን። በተጨማሪም፣ አዲሱ መጽሐፋቸው በሚያነሳቸው ጥያቄዎች ዙሪያ፣ ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የወደፊት አቅጣጫ፣ ስለ ሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ እና በዚህ ፈጣን የለውጥ ዘመን ኢትዮጵያ ሊኖራት ስለሚችለው ሚና በጥልቀት እንቃኛለን። ⸻ This week’s guest is Solomon Kassa, a technology consultant, author, and the creator and host of the popular television program TechTalk with Solomon. For years, Solomon has made complex scientific and technological ideas accessible to Ethiopian audiences in Amharic, helping bridge the gap between rapid innovation and everyday understanding. With a background in software engineering and technology consulting, Solomon brings together technical expertise and a commitment to public education. Through his television program, his writing, and his public talks, he has encouraged young Ethiopians to see themselves not only as consumers of technology but as innovators who can help shape its future. This episode coincides with the release of Solomon’s new book, “Artificial Intelligence: The Last Invention or the End of Invention?” Written in Amharic over two years of research and writing, the book explores one of the defining technologies of our time. Its title poses a timely question: will artificial intelligence open a new chapter for human creativity, or will it mark its end? In this episode, we talk about Solomon’s journey in technology and his perspective on innovation. We also discuss the ideas behind his new book: the future of artificial intelligence, the changing relationship between humans and technology, and the role Ethiopia and the next generation can play in this fast-moving era. Resources https://www.solomonkassa.com/ Contact Information Email: solokassa.ai@gmail.com Phone: 0966915226 or 0912792421