ናፍቃለሁ Cover Song With Lyrics Orginal Mezmur By Abraham Halake
MENORAH WORSHIP
0:00 / 0:00
ናፍቃለሁ Cover Song With Lyrics Orginal Mezmur By Abraham Halake
506 просмотров · 9 дн. назад
MENORAH WORSHIP
1,04 тыс. подписчиков
506 просмотров · 9 дн. назад
ናፍቃለሁ Cover Song With Lyrics Orginal Mezmur By Abraham Halake
መቼ ትሆን ያቺ ቀን ምንገናኝባት
ከተወጋልኝ ጋር ፊት ለፊት ምንተያይባት
ከቀን ወደ ቀን ናፍቆቴ በርትቶብኛል
ሁል ጊዜ ሳብሰለስል እረፍትን ነስቶኛል
አዝ፦
ናፍቃለሁ ላይህ እሻለሁ
ሞተህ ያዳንከኝን ላይህ እናፍቃለሁ።
ናፍቃለሁ ላይህ እሻለሁ
ቤዛ የሆንከኝን ላይህ እመኛለሁ።
ናፍቃለሁ ላይህ እሻለሁ
በደምህ የገዛኸኝን ላይህ እናፍቃለሁ።
ናፍቃለሁ ላይህ እሻለሁ
ሕይወት የሆንከኝን ላይህ እመኛለሁ።
ያኔ ደስታዬ ሙሉ/ፍጹም ይሆናል
ሁልጊዜ አይኖቼ አንተን ያዩሃል
ምንም ነገር እኔን አያረካኝም
ምነው በኖረኝ ብዬ አያስመኘኝም
የእኔ ናፍቆት የእኔ ጉጉት የሆነው
ሞቶ ያዳነኝን ፊቱን ማየት ነው
ሰው ብዙ ነገር እጅግ ያስጨንቀዋል
በቀን በማታ እንቅልፉን ይነሳዋል
የእኔ ናፍቆት የእኔ ጉጉት የሆነው
ሞቶ ያዳነኝን ፊቱን ማየት ነው