የእርግዝና 7ኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of week 7 pregnancy
ጤና Cure
0:00 / 0:00
የእርግዝና 7ኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of week 7 pregnancy
30 746 просмотров · 3 г. назад
ጤና Cure
203 тыс. подписчиков
30 746 просмотров · 3 г. назад
በዚህ ጊዜ፣ እርጉዝ መሆናችሁን አውቃችኋል። ነገር ግን አንዳንድ ሴቶች እስከዚህ ሳምንት ድረስ በእርግጠኝነት እርጉዝ መሆናቸውን አያውቁም። በተለይም ደግሞ ምርመራ ካላደረጉ። በዚህ ጊዜ ምናልባት ክብደት ልትቀንሱ ትችላላችሁ። በተለይም በጠዋት ህመም ምክንያት ክብደታችሁ ሊቀንስ ይችላል።
ጡቶቻችሁ እያደጉ ይሄዳሉ። ልብስ በምትለብሱበት ጊዜ ምቾት ላይሰማችሁ ይችላል።
📌ፅንሱ ምን ይመስላል ?
ልጃችሁ በዚህ ሳምንት ወደ 1/4 ኢንች ርዝመት አለው እና አሁንም እንደ ፅንስ ይቆጠራል። ትንሹ የአከርካሪ ጅራቱ እየቀነሰ ይሄዳል እና ብዙም ሳይቆይ ይጠፋል። በዚህ ሳምንት የልጁ ጭንቅላት እና ፊት እያደገ ነው። የአፍንጫ ቀዳዳዎቹ ይታያሉ እና የዓይን ሌንሶች መፈጠር ይጀምራሉ። መቅዘፊያ የሚመስሉት እጆቹ እና እግሮች እንዲሁ ይፈጠራሉ።
📌የ 7 ሳምንት የእርግዝና ምልክቶች
በዚህ ሳምንት የምታዩት የእርግዝና ምልክቶች ከዚህ በፊት ባሉት ሳምንታት ካያችኋቸው ምልክቶች ጋር አንድ ናቸው። ነገር ግን ይበልጥ ግልፅ እየሆኑ የሚመጡበት ሳምንት ነው። እናም እነዚህ ምልክቶች የሚያበሳጩ ወይም አድካሚ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህም
➣ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ
ምልክቶቹ በጣም ከባድ ከሆኑ እና ምንም አይነት ምግብ ወይም ፈሳሽ ከ24 ሰአታት በላይ ማቆየት ካልቻልቻላችሁ የሃይፐርሜሲስ ግራቪዳረም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ህክምና ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህም ማለት በጣም የከፋ የጠዋት ሕመም ነው።
➣ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
➣ የጡት ጫፎች መጥቆር
➣ ድካም
➣ የምግብ ጥላቻ እና አምሮት
የምግብ ጥላቻ እና ማቅለሽለሽ በእርግዝናችሁ ጊዜ ሁሉ ሊቆይ ይችላል ነገር ግን ለአብዛኛዎቹ ሴቶች ከመጀመሪያው ሶስት ወር በኋላ ይቀንስላቸዋል።
➣ መለስተኛ ዳሌ ህመም
➣ከመጠን በላይ ምራቅ ማመንጨት
ከመጠን በላይ ምራቅ በዚህ ሳምንት ሊያጋጥማችሁ የሚችል የሚያበሳጭ ምልክት ነው። ለዚህም ምክንያቱ የሆርሞኖች ለውጥ ሊሆን ይችላል። ስኳር የሌለው ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላዎችን በመምጠጥ ስሜቱን መቀነስ ትችላላችሁ። ብዙ ውሃ መጠጣትም አስፈላጊ ነው።
➣ ድካም
በመጀመሪያዎቹ እና በሦስተኛው ወር አጋማሽ ላይ ድካም የተለመደ ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት የፕሮጀስትሮን ሆርሞን በሰውነታችሁ ውስጥ እየጨመረ ስለሚሄድ ነው። በዚህም ምክንያት እንቅልፍ እንቅልፍ ይላችኋል። ለዚህም መተኛት ወይም እረፍ ማድረጉ ጥሩ መፍትሄ ነው። ጉልበትን ለመጨመር ሌላኛው መንገድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ነው።
➣ቀላል እና ነጠብጣብ የደም መፍሰስ
ቀላል እና ነጠብጣብ የደም መፍሰስ መደበኛ እና በዚህ የእርግዝናችሁ ሳምንት ሊያጋጥማችሁ የሚችል ምልክት ነው። በተለይም ደግሞ ግንኙነት ካረጋችሁ በኋሏ።
📌በዚህ ሳምንት ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች
➣ሰፋ ያሉ እና የማያጣብቁ እንዲሁም ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ ይኖርባችኋል። ይልም ምቹነት እንዲሰማችሁ ያደርጋል።
➣ለእናንተም ለልጃችሁም አስፈላጊውን ንጥረ ነገር እንድታገኙ ጤናማ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባችኋል። እንዲሁም የቅድመ ወሊድ ቫይታሚን በሀኪም ትዕዛዝ ብትወስዱ ጥሩ ነው።
➣እንዲሁም በቂ ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይኖርባችኋል።
#pregnancy
#youtube
#education