ዶ/ር ደረጀ ከበደ | የማሚቱ እሪታ |ድንዛዜ| #lyrics |Dr. Dereje Kebede| denezaze| #Kidus_Melody
Kidus Melody
0:00 / 0:00
ዶ/ር ደረጀ ከበደ | የማሚቱ እሪታ |ድንዛዜ| #lyrics |Dr. Dereje Kebede| denezaze| #Kidus_Melody
12 780 просмотров · 2 мес. назад
Kidus Melody
4,23 тыс. подписчиков
12 780 просмотров · 2 мес. назад
#lyrics #kidusmelody #derejekebede
ደመናው ምን አለ?ምን አለ ንፋሱ?
ያው ካፍያ ያው ዝናብ አያሻማም መልሱ
ጊዜ ብቻ ቀረ የሚያነበው የለም ወቅቱን የሚረዳ
እዚህ ለቅሶ ድንኳን እዛ ፈንጠዝያ ለወቅቱ ባዳ
ህዝብ ድንዛዜ ቢሰፈር አያልቅም
ያደበተው እንቅልፍ ሰመመኑ አይለቅም
ምነው ወቅቱ ከፍቶ ሬሳ ክምር ሲሆን
ምነው አንተክዝ ምነው ሩህሩህ አንሆን
ምነው አይሰማን የማሚቱ እሪታ
በአባቷ ሬሳ ጎን ስትጮህ ተደፍታ
ምነው ማረን አንል ምነው ኪራላይሶ
ፍትህ ምች መቷት ፍርድ ተቀልብሶ
የያዘን አባዜ ዝርያው እንግዳ
አዚሙ የማይረክስ ጭፍን የሚነዳ
የጎረቤት ለቅሶ ኡኡታው ቢቀልጥም
ሀዘን ካላንኳኳ ጆሯችን አንሰጥም
ተንጠን ሆ ብለን አይበቃንም ምነው
ድረሱልን ባዪን ዛሬም አልሰማነው
ድንዛዜ
የዘመኑ ክስተት ማን ይማር ከስህተት
ድንዛዜ የያዘን አባዜ
ቤቴን ካልደፈሩ የትም ይመንጥሩ
ወዳጅ በመከራ አንሰማው ቢጣራ
ድንዛዜ
የያዘን አባዜ
ክፉ ዘመን ክፍ መጥቶ መች ይሄዳል
ዳሩ ስሜተኛ ወቅቱን መች ይረዳል
ዛሬም በር ዘግተን ስንዘል ታችና ላይ
የስሜት ጀሌዎች ዙሪያችን አናይ
ውሎ መግባት እንኳን ብርቅ ነው ይላሉ
የደጆቹ ሰዎች ካጥር ውጭ እያሉ
የተሳከረ ህዝብ በነሲብ ይጓዛል
በተኩላዎች ፉጨት በጥቂት ይዋዛል
ወንጌል ለምኔዎች ቅዱሱን ቃሉን ሸሹ
ከበሮና ሆታ ያለበትን ሲሹ
ሳምንት ሄዶ ሳምንት የህዝብህ ግላቱ
ኦና ቤት ነው ማለት አንተ የለህ ቤቱ
ድንዛዜ
የያዘን አባዜ
የዘመኑ ክስተት
ማን ይማር ከስህተት
በመብረቅ ብልጭታ ወይ በጎመራ እሳት
በጥሪኝ ሽታ ባጋም እሾህ ውጋት
በአለንጋ ጫፍ ፉጨት ወይ በባሩድ ሽታ
ቀስቅስ የተኛውን ነጋሪቱን ምታ
ሱባኤ የሚገቡ የሚየለቅሱ ጠፉ
በስጋና በነፍስ ባመፅ ለተገፉ
የወገን የሃገር ሰቆቃ አይሰማው
አማኝ ይቧርቃል ተጨንቋል ከተማው
ዙሪያውን የማይቃኝ ህልውና ለራስ
የዘንድሮ ወንጌል ከራስ በላይ ነፋስ
ድንዛዜ
የያዘን አባዜ
የትም ይመንጥሩ ቤቴን ካልደፈሩ
ወዳጅ በመከራ አንሰማው ቢጣራ
ሺህ ወድቆ ጎናችን ፍንክች ልባችን
ድንዛዜ
ፍቅራችን ማነው የነጠቀን ?
ድንጋይ ልብ አጨናነቀን
መቼ ነው የፈውሳችን ቀን?
©ዘማሪ ዶ/ር ደረጀ ከበደ