Перейти к содержимому

በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ወደ ምርት ማስገባት ለግብርና ምርታማነትን ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

Amhara Agriculture Bureau

0:00 / 0:00

በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ወደ ምርት ማስገባት ለግብርና ምርታማነትን ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

346 просмотров · 4 месяца назад
Amhara Agriculture Bureau
1,44 тыс. подписчиков
346 просмотров · 4 месяца назад
ባህርዳር፣ ሰኔ 9፣ 2018 ዓ/ም ( ግብርና ቢሮ ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስተዋወቅ ይቻል ዘንድ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ የምርምር ተቋሙ ቴክኖሎጂን ማፍለቅና ማላመድ፣ ማስተዋወቅ እንዲሁም የመነሻ ዘር ብዜት ማካሄድ ዓለማ አድርጎ እንደሚሰራ ጠቅሰው በክልሉ ከ188 በላይ ዝርያዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። እነዚህን ዝርያዎች ማስተዋወቅ ከተቻለ በምርታማነት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል። ወደ ሰርቶ ማሳያ የሚገቡ ዝርያዎችን ለይተን ወደ ተጨባጭ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ ስለመሆኑ አንስተዋል። አዳዲስ ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ወደ ምርት ማስገባት የግብርና ምርትማነትን ያሳድጋል ሲሉ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ምርምር ተቋም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀኝአዝማች መስፍን በበኩላቸው የግብርና ዘርፉን ከልማዳዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ አሰራር ለማሸጋገር ሰርቶ ማሳያ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው አርሶ አደሩ በተግባር አይቶ የሚማርበት መሆኑንም አንስተዋል። የምርምር ተቋሙ፣ ምርጥ ዘር አባዥ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች በጋራ ተቀናጅተው አማራጭ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ማቅረብ እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከምርታማነት፣ ከገበያ ተፈላጊነት፣ በሽታንና ድርቅን ከመቋቋም እንዲሁም ለስርዓተ ምግብ ካለው ፋይዳ አንፃር አማራጭ ዝርያዎች በስፋት ለማቅረብ ያሉ አቅሞችን አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል። አቶ ቀኝአዝማች መስፍን አክለውም ተቀናጅተን ስንሰራ ችግሮች ይፈታሉ፣ ውጤት እናስመዘግባለን፣ ቅንጅታዊ አሰራርም ይጎለብታል ሲሉ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ( CREW ) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አግደው ሞላ ለመወያያ የሚሆን መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሌሎች አቅራቢዎችም የውይይት መነሻ ፅሁፍ በማቅረብ ገንቢ ውይይት ተደርጓል። በስልጠናና ምክክር መድረኩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች፣ የምርምር፣ የዘር አባዥ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ተሳታፊ ሆነዋል። ዘጋቢ:- አንተነህ ሰውአገኝ ድምፅ ምስል ቅንብር ኤዲተር : ጌታቸው ታፈረ